ስለ እኛ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን እንደገና ለማዋቀር ባወጣው አዋጅ ቁጥር 84/2016 ከተዋቀሩ አስፈፃሚ አካላት አንዱ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ነው፡፡

መስሪያ ቤቱ በሁለት ዘርፍ ተዋቅሮ በአራት ዳይሬክቶሬቶች እና በአስር ቡድኖች በማዕከል ደረጃ የሚመራ ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ ዘመናዊ የመንግስት ህንጻና ንብረት አስተዳደር ስርዓት በመዘርጋት ወጥና ስታንዳርዱን የጠበቀ፣ ደህንነታቸው የጠበቀ ፣ፅዱና ምቹ የሆነ ምድረ ግቢ ያላቸው ህንፃዎችን በማልማት ቀልጣፋና ውጤታማ የአሰራር ስርዓት እንዲኖር የቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት ከብክነት የፀዳ የንብረት አስተዳደር ስርዓት ማስፈን ነው፡፡ በተጨማሪም የህንፃና የንብረት አስተዳደር ስርዓቱን ለማዘመን፣የተደራጀ ተዓማኝነት ያለው የመረጃ አያያዝ ስርዓት ስራ ላይ ለማዋል፣ ንብረቶችን ለታለመለት ዓላማ እንዲውል በማድረግ የሀብት ብክነትን በመከላከል ፍትሃዊ የሆነ የሀብት አጠቃቀም የከተማ አስተዳደሩን ህንፃዎችና ንብረቶች የማስተዳደር፣ የመቆጣጠር፣ የመከታተል፣ የቢሮ መገልገያ እቃዎች ስታንዳርዶችን የማዘጋጀትና የማስተግብር፣ዘመናዊ የንብረት አስተዳደር አሰራሮች የማስተግበር ፣የአቅም ግንባታ ስራዎች በማከናወን ለከተማ አስተዳደሩ የቴክኒክና ሙያዊ ድጋፍ የመስጠት ስራዎችን የሚያከናውን ተቋም ነው፡፡

ተግባርና ኃላፊነት

1. በመንግስት ህንጻና ንብረት አስተዳደር ላይ ለከተማ አስተዳደሩ የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፤ ያማክራል፤

2. ስልጣኑ በህግ ለሌላ አካል ወይም ለሌላ የመንግስት መስሪያ ቤት ካልተሰጠ በቀር የከተማውን አስተዳደር ህንፃዎችንና ቋሚ ንብረቶችን ይመዘግባል፤ በበላይነት ያስተዳድራል፤ ያድሳል፤ ጥገና የሚያስፈልጋቸውን ህንፃዎች በመለየት እንዲጠገን ያደርጋል፤

3. የህንጻና ንብረት አስተዳደር እና አጠቃቀም ዘመናዊ ስርዓትን ይዘረጋል፤ ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ያረጋግጣል፤ ምድረ ግቢን ውብና ማራኪ እንዲሆኑ ያደርጋል፤

4. የመንግስት ህንፃዎች አጠቃቀም፣ ለተጠቃሚው ያላቸው ተደራሽነት እና ከወጪ አንፃር ውጤታማ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤

5. የተቋማትን ፍላጎት፣ የስራ ባህሪይ እና የተገልጋይ ሁኔታን በማጥናት የተቋማትንና የስራ ክፍሎችን የስራ ቦታ ይደለድላል፤

6. የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ተቋማት ለአገልገሎት አሰጣጥ የሚያስፈልጋቸውን ህንፃዎች የኪራይ ደረጃ አጥንቶ ይወስናል፤ ለመንግስት አገልግሎት የሚውሉ ህንፃዎች እንዲገነቡ ያደርጋል፤

7. በከተማው ውስጥ ባለቤት የሌላቸው ህንጻና ንብረቶችን አግባብ ባለው ህግ መሰረት ተረክቦ ያስተዳድራል፤

8. የመንግስት ህንፃዎች ወጥ የሆነ ስታንዳርድ እና ዲዛይን እንዲኖራቸው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ይሰራል፤ ያስገነባል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤

9. የህንጻ አስተዳደር ሥራዎች የተቀላጠፉና ውጤታማ እንዲሆኑ የውስጥ አደረጃጀት እና የቢሮ ቁሳቁስ ስታንዳርድ ያዘጋጃል፤ እንዲተገበር ያደርጋል፤

10. በመንግስት የንብረት አያያዝ ስርዓት መሰረት የመንግስት ንብረቶች በአግባቡ ስለመያዛቸው እና ጥቅም ላይ ስለመዋላቸው የንብረት ኦዲት ያደርጋል፤

11. በባለስልጣኑ የህንፃና ንብረት ኦዲት ውጤት መሰረት ተገቢውን የእርምት ዕርምጃ ያልወሰዱ የመንግስት መ/ቤቶችን ለይቶ ተጠሪ ለሆነለት ቢሮና ለሚመለከተው አካል ያሳውቃል፤

12. አግባብ ባለው ህግ ቋሚ ንብረቶች ዋጋ እንዲወጣላቸው እና በየዓመቱ የዕልቀት ዋጋ እንዲሰላላቸው በማድረግ መንግስት የቋሚ ንብረቶች የያዙትን ዋጋ እንዲያውቅ ያደርጋል፤

13. ባለስልጣኑ በሚያስተዳድራቸው ንብረቶች ላይ የሚፈጸሙ ህገወጥ ድርጊቶችን ይከላከላል፤ ተፈጽሞም ሲገኝ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፤

14. የመንግስት ህንፃዎች የሚገነቡበት ቦታ ያስፈቅዳል፤ ይመዘግባል፤ ተገቢውን የይዞታ ማረጋገጫ እና የግንባታ ፈቃድ እንዲሰጥ ያደርጋል፤ ይጠብቃል፤

15. የመንግስት ህንፃዎች የሰራተኞች ካፍቴሪያ፣ የጽዳትና ውበት፣ የጥበቃ፣ የመጀመሪያ ህክምና፣ የመንግስት ተሸከርካሪዎች ማቆሚያ፣ የመኪና እጥበት እና የህፃናት ማቆያ አገልግሎቶች ተግባራትን ያከናውናል፤

አድራሻ

የቢሮ አድራሻ:

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ፒያሳ እሳት አደጋ ስራ አመራር ፊት ለፊት የሽሮ ሜዳ ታክሲ ማውረጃ አበባዬ/ራህመት ታቦር ህንፃ ከ5ኛ ወለል ጀምሮ በሚገኘው ቢሮ ይሆናል፡፡

ስልክ:

0114705811

Loading
Your message has been sent. Thank you!